አርባምንጭ ከተማ ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱ ተረጋገጠ
አርባምንጭ ከተማ በ2018 የውድድር ዘመን ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱ ተረጋግጧል።
አዞዎቹ ወደ ታችኛው ሊግ መውረዳቸውን ያረጋገጡት በ36ኛው ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በፋሲል ከነማ 2ለ0 በመሸናፋቸው ነው።
ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለአፄዎቹ ሁለቱንም የማሸነፊያ ጎሎች ታምራት እያሱ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ በ2016 የውድድር ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ተመልሶ ሲሳተፍ የነበረው አርባምንጭ ከተማ ለሁለት ዓመታት በዋናው የሊግ ዕርከን ሲሳተፍ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ሁለት ቀሪ ጨዋታዎች እያሉት ወደ ከፍተኛ ሊጉ መውረዱ ተረጋግጧል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ