ዴክላን ራይስ የአርሰናል የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመረጠ
እንግሊዛዊው አማካይ ዴክላን ራይስ የአርሰናል የውድድር ዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጧል።
ዴክላን ራይስ መድፈኞቹ ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚዬር ሊጉ ሻምፒዮን ሲሆን እና ከ20 ዓመታት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለፍፃሜ ሲደርስ ባሳየው አስደናቂ 44 በመቶ ድምፅ በማግኘት ተመራጭ ሆኗል።
ተጫዋቹ ዴቪድ ራያን እና ጋብርኤል ማጋሌሽን በማስከተል ነው ተመራጭ የሆነው።
ዴክላን ራይስ ባለፈው ዓመትም የዚህ ሽልማት አሸናፊ እንደነበር አይዘነጋም።
በዚህም ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠ 6ኛው የአርሰናል ተጫዋች ሆኗል።
ዴክላን ራይስ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለሰሜን ለንደኑ ክለብ በሁሉም ውድድሮች 5 ጎል አስቆጥሮ 9 ግብ የሆኑ ክሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ
ዴክላን ራይስ የአርሰናል የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመረጠ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ