በከምባታ ዞን ሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርአት (E-LMIS) ምዝገባ በይፋ መጀመሩን የከተማው ኢንተርፕራይዝና ሥራ ዕድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት አስታወቀ
በከተማው የወጣቶች ሥራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ እና የሥራ ዕድል ፈጠራን ግልፅ፣ ፍትሐዊና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችል የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርአት (E-LMIS) የባዮሜትሪክስ ምዝገባ በይፋ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
ዘመናዊ የባዮሜትሪክስ ምዝገባ ትክክለኛ ሥራ ፈላጊዎችን በመለየት የሥራ ዕድልና የገበያ ትስስርን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመምራት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት በሺንሽቾ ከተማ አስተዳዳር ኢንተርፕራይዝና ሥራ ዕድል ፈጠረ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ስጦታ ደገሎ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርአት (E-LMIS) ቴክኖሎጂ ሠራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) ለመስጠት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ለማመቻቸት፣ የሪሞት ሥራዎችንና የኢ-ኮሜርስ ተጠቃሚነትን ለማስፋፋት ብሎም ዲጂታል ኢንተርፕራይዞችን ለማደራጀት ከፍተኛ አጋዥ መሆኑንም አቶ ስጦታ ገልፀዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ሥራ የሚፈልጉ አካላት ከአጭር እስከ ረጅም ጊዜ የሚወስዱ የተለያዩ ስልጠናዎች የሚያገኙበትን መንገድ እንደሚያመቻች ኃላፊው አብራርተዋል፡፡
ዘመናዊ የባዮሜትሪክስ ምዝገባ ትክክለኛ ሥራ ፈላጊዎችን በመለየት የሥራ ዕድልና የገበያ ትስስርን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመምራት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርአት (E-LMIS) ቴክኖሎጂ ሠራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) ለመስጠት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ለማመቻቸት፣ የሪሞት ሥራዎችንና የኢ-ኮሜርስ ተጠቃሚነትን ለማስፋፋት ብሎም ዲጂታል ኢንተርፕራይዞችን ለማደራጀት ከፍተኛ አጋዥ መሆኑንም የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ስጦታ ገልፀዋል፡፡
በሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር የቄጣለ ማዕከል (E-LMIS) ባለሙያ አቶ ፍጹም አበበ እንደገለጸት መረጃ ስርዓቱ እንደ አዲስ ለሚደራጁ ከፋይናንስ ተቋማትና ከአለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር በጋራ ቅንጅት በመፍጠር በቀላሉ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙበትን አሰራር እንደሚያመቻች ጠቅሰዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ሥራ የሚፈልጉ አካላት ከአጭር እስከ ረጅም ጊዜ የሚወሰዱ የተለያዩ ስልጠናዎችን የሚያገኙበትን መንገድ እንደሚያመቻች አብራርተዋል፡፡
የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ሲመዘገቡ የነበሩ አካላት በበኩላቸው የአገልግሎቱን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በመረዳት መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) መለያ ቁጥር አዲስ ስራ በሚፈለግበት ጊዜ ከዚህ ቀዳም ሲስተዋል የነበረውን ችግር የሚቀርፍ በመሆኑ ማንኛውም ሥራ ፈላጊ በመመዝገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: ደሣለኝ ታደሠ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ተደረገ
ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ጨምሮ ለእሳት አደጋ መንስኤ የሚሆኑ የመጠቀሚያ ዕቃዎችን በጥንቃቄ በመጠቀም በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ
በሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) የተመራል ኡክ በወላይታሶዶ ዩኒቨርሲ ቲየባዮ ጋዝ ማምረቻ ፕሮጀክትን የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ አደረገ