ባለፋት ሶስት አመታት በክልሉ በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉበኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ባለፋት ሶስት አመታት በክልሉ በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉበኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ገለጹ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ አመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉበኤዉን እያካሄደ ይገኛል።
ጉባኤውን በይፋ ያስጀመሩት አፈ ጉባኤዋ፤ በክልሉ ባለፉት ሶስት አመታት በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።
አፈ ጉበኤዋ እንዳሉት፤ ጉባኤውን ከቀደሙት ጉባኤዎች ልዩ የሚያደርገው ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ስትጠብቀውና ስትመኘው የቆየችውን ሀገራዊ ምክክርን በይፋ የጀመረችበት ታሪካዊ ወቅት ላይ በመሆኑ ነው።
ምክር ቤቱ ባለፋት ሶስት አመታት ቆይታ ካከናወናቸው አብይ ተግባራት መካከል የክልሉን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የብሄረሰቦች ምክር ቤት የጋራ ጉባኤ በማካሄድ የክልሉን ህገ መንግስት በአዲስ መልክ ማፅደቅ፣ የህግ አውጪ፣ የህግ ተርጓሚና የህግ አስፈፃሚ አካላት ሹመት ማፅደቅ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆነው ለቆዩትን የአደረጃጀት ጥያቄዎች ምላሽ አንዲያገኙ ማድረግ እንደሆነ አብራርተዋል።
አፈ ጉባኤዋ አያይዘውም ምክር ቤቱ የህዝብ ዉክልና ተግባራትን በመፈፀም ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኙ መደበኛ እና ድንገተኛ የመስክ ክትትልና ቁጥጥር አድርጓል ብለዋል።
ባለፋት ሶስት አመታት በክልሉ በግብርናው ዘርፍ የህዝብን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባሻገር ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር የተደረጉ ጥረቶች ውጤታማ መሆናቸውን አፈ ጉበኤዋ ገልፀዋል።
በመሰረተ ልማት ዘርፎች የተጀመሩ የመስኖ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ እና ማህበራዊ ተቋማት ፕሮጀክቶች ልዩ ትኩረት በመሰጠት ተመርተዋል ያሉት ወ/ሮ ፋጤ፤ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ፈጥነው እንዲጠናቀቁ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
ሰው ተኮር ስራዎች ውጤት ማስገኘታቸውን የጠቀሱት አፈ ጉባኤዋ፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመር፣ የከተማ ኮሪደር ልማት፣ የከተማ ኢንሼቲቮች ተጨባጭ እድገት የተመዘገበባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ መለሰች ዘለቀ

More Stories
የመረጃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተቋሙ ሰራተኞች በአደረጉት ጥረት የተሻለ ውጤት መመዝገቡን በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚዛን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የ2018 ዓ.ም ክልላዊ የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መነሻ ያሉባቸውን ክፍተት በአዲሱ 2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለመሻገር በልዩ ቁርጠኝነት እንደሚሠሩ የየዞኑ የትምህርት አመራሮች ገለፁ
ኒውካስል ዩናይትድ ብሩኖ ጊማሬሽን በ75 ሚሊዮን ፓውንድ ለአርሰናል ለመሸጥ ተስማማ