የገፀ- በረከቶች ባለቤት- ጎፋ
ጎፋ ብዙ ገፀ- በረከቶች ያሉበት ዞን ነው። ለማዕከላዊ ይሁን ለዓለም ገበያ የሚቀርቡ እንደ ሰሊጥ፣ ተልባ፣ ቡና እና በቆሎን ጨምሮ ጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች ይመረቱበታል፡፡ የአካባቢው ልምላሜ አዕምሮና መንፈስን ያድሳል፡፡
በአጠቃላይ ተፈጥሯዊ ውበት የተላበሰ እና በግብርና ምርቶች የተሞላ ዞን ነው፡፡ እኛም በዓመቱ በዞኑ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና በቀጣይ መቀረፍ ያለባቸው ችግሮች ምንድን ናቸው? ስንል ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ጌትነት በጋሻው ጋር ቆይታ አድርገን ነበር፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እንደሚሉት የዞኑ ትልቁ አቅም እርሻ ወይም ግብርና ነው።
ይህም በመኸርና በበልግ መልማቱን ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት በገጠመው የዝናብ መቆራረጥ ምክንያት አካባቢው በድርቅ መጎዳቱን ያስታውሳሉ፡፡ ይህንን ለመቋቋምና መልሶ ለማልማት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
ህዝቡን በማስተባበር ጊዜ ተወስዶበት ሲሰራ እንደቆየ ገልፀው በድርቁ ምክንያት ህይወቱን ያጣ ሰው እንደሌለና እነዚህን ከባድ ጊዜያት በተለያየ መልኩ ማሳለፍ መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡ በዘንድሮ ዓመት የነበሩ ችግሮች ታልፈው በበልግ ስኬታማ እና ጥሩ ውጤት ማምጣት መቻሉን ዶ/ር ጌትነት ይናገራሉ፡ ፡
ደረቅ በሆኑ ቦታዎች ላይ መተከል የሚችሉ ማሽላ፣ በቆሎ፣ የመሳሰሉ የመልካሳ የገፀ- በረከቶች ባለቤት ዝርያዎችን በስፋት በማቅረብ አርሶ አደሩ የበልግ ውጤቱን ለማካካስ ተሞክሯል ይላሉ፡፡ በአጠቃላይ በበልግ እርሻ ከ3.6 ሚሊየን ኩንታል በላይ በሰብል፣ በስራስር እና በሌሎች አዝርዕቶች ውጤት ማምጣት ተችሏል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ የደረሰበትን ጉዳት ሊያካክስ በሚችል የበልግ ስራዎች መሰራታቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ከ350 ሄክታር በላይ የበጋ መስኖ ስንዴ የታረሰ ሲሆን ከዚህም ትምህርት ተወስዶ ግብርናውን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በመኸር ላይ ርብርብ ለማድረግ የማሳ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል፡፡
ለመኸር እርሻ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት የሚያስፈልገው 60 ሺህ ኩንታል ሲሆን ከቀድሞ ያደረ ከ12 ሺህ ኩንታል በላይ መኖሩንም ዋና አስተዳዳሪው ይናገራሉ። የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር ቢገጥም እንኳን ኮምፖስት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
በዞኑ አጠቃላይ በመኸር 78 ሺህ ሄክታር፣ በበልግ 62 ሺህ ሄክታር መሬት ስለሚለማ ትልቁ ሀብታችን የግብርና ስራችን በመሆኑ ትኩረት እንሰጣለን ብለዋል፡፡ በመስኖ የሚለሙ ማሳዎችም በኡባ ደብረ ፀሐይና ደንባ ጎፋ አካባቢ እንዳሉ ነው የተናገሩት፡፡ መንገድ የዞኑ ቁልፍ ችግር መሆኑንና ዋናው መንገድ ከሶዶ እስከ ሳውላ የሚሰራውም በጥሩ ሁኔታ እየተገነባ ሳለ እንደተቋረጠ ጠቁመዋል። በፍጥነት ግንባታውን ለማስጀመርም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ
እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በአንጻሩ በበጀት ዓመቱ ለብዙ ዓመታት የመልካም አስተዳደር ችግር ሆነው የቆዩ ድልድዮች ተጠናቀው ለህብረተሰቡ ክፍት መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡ የተጀመሩ ስራዎችን ለማስጀመር ማሽነሪ እና የበጀት አቅም ስለሚፈልግ እንደ ክልልም ትኩረት ተሰጥቶበት ስራዎች መጀመራቸውን ነው ዋና አስተዳዳሪው የተናገሩት፡፡ በበጀት ዓመቱ ዞኑ ወደ አምስትና ከዚያ በላይ የቢሮ መሰረተ ልማት ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ነው የገለጹት፡፡
በወረዳም ይሁን በከተማ አስተዳደር የልማት ስራዎች ታቅደው በመንግስት በጀትና በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረው፣ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ከመብራትም ጋር ተያይዞ የትራንስፎርመር ዝርጋታ ተደራሽ ባልሆኑ አካባቢዎች የማድረስ ስራዎች መሰራታቸውን ነው ዋና አስተዳዳሪው የተናገሩት፡፡
በዞኑ የኔትወርክ ሽፋን ያልደረሰባቸው በርካታ ቀበሌያት አሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በኢትዮ ቴሌኮም የሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ዶክተር ጌትነት ገልጸዋል፡፡ ከማህበራዊ ዘርፍ አኳያ ትምህርትና ጤና ቁልፍ ሴክተሮች ሲሆኑ ትምህርት ላይ እንደ ሀገር የጥራት ችግር መኖሩን፣ በዞኑም ይህ ችግር ተስተውሏል ነው ያሉት።
ችግሩን ለመፍታት ባለድርሻ አካላትን በማወያየትና ተማሪዎችን በማሳተፍ ለተማሪዎች ውጤታማነት የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል፡፡ ትምህርት ቤቶችን ከማጠናከር አንፃር ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት በበጀት ዓመቱ ጅምሩ ጥሩ ሆኖ ጥራት እንዲመጣ በዞኑ ልማት ማህበር አማካይነት ሞዴል ትምህርት ቤት ተገንብቶ ተማሪዎችን የማስተማር ስራዎች ተጀምረዋል ብለዋል፡፡
በዚህም ከተለያዩ ትምህርት ቤቶችና ወረዳዎች ከፍተኛ ነጥብ ያላቸው ተማሪዎች ተለይተው እንዲማሩ መደረጉን አስረድተዋል። ከጤና አኳያም ተቋማትን ማጠናከር እና አገልግሎትን ውጤታማ ማድረግ በተለይም ሆስፒታሎች ላይ ቁሳቁስ ለማሟላት ጥረት መደረጉን ነው የተናገሩት፡፡ የደም አቅርቦት በጤና ተቋማት እንደ ችግር ስለሚነሳ ከሳውላ አርባምንጭና ወላይታ ሶዶ የሚኬድ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ ከክልሉ መንግስት ጋር በመነጋገር የደም ባንክ ግንባታ ስራው እየተጠናቀቀ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ነገር ግን ማሽነሪና ለደም ባንኩ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን በቀጣይ ለማሟላት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሚናገሩት ዋና አስተዳዳሪው፣ በዚህም አንድም እናት በደም እጥረት ምክንያት እንዳትሞት ስራዎች በትኩረት መሰራታቸውንም አያይዘው ገልፀዋል፡፡
ይህም ስራ በዞኑ መንግስት ብቻ ሳይሆን ከክልልም አልፎ የፌደራል መንግስት ድጋፍ የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በጤናው ዙሪያ ያለው ትልቁ ተግዳሮት ቅድመ መከላከል ወይም የጤና ኤክስቴንሽን ስራዎች ውጤታማ አለመሆናቸው ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረውን የወባ እና የኮሌራ ወረርሽኞችን ለመቀልበስ ተችሏል፡፡
የገቢ እና የኢኮኖሚ አቅምን ከማሳደግ አንፃር ትልቁ ስራ ዞኑ ወጪውን በራሱ ገቢ መሸፈን አለበት ከሚል እሳቤ የገቢ አቅሙን 70 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱን ተናግረው፣ ከዚህም አንፃር ከ748 ሚሊየን 378 ሺህ 414 ብር ከ76 ሳንቲም መሰብሰቡን ይገልጻሉ፡፡
ዞኑ ለዓለም ገበያ የሚቀርቡ እንደ ቡና ያሉ ምርቶችን ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ ይታወቃል። በ2ዐ15 ዓመት 2 ሺህ ቶን ቡና ለማቅረብ መታቀዱንም ነው የተናገሩት፡፡ እስካሁንም 1 ሺህ 800 ቶን ቡና ስለመቅረቡ ይገልጻሉ፡፡ በአሪቲ ልማትም ዘንድሮ ለማዕከላዊ ገበያ ከ10 ሺህ ቶን በላይ ቀርቧል፡፡ ከዚህም ውስጥ 4 ሺህ 50 ቶን ለውጪ ገበያ መቅረቡን ነው የተናገሩት።
ክልሉ በሰጠው ግብረመልስ የተሻለ ገቢ ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦ አድርጓል ነው ያሉት፡፡ ሰሊጥንም ለውጪ ገበያ፣ እንዲሁም ኮረሪማ ለማዕከላዊ፣ ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገበያ የማቅረቡ ስራዎች ስለተጀመሩ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል፡፡
የሳውላ ከተማ ከንቲባ አቶ ኤርሚያስ ስላሏቸው÷ ለቢሮ ስራ ያላቸው ትኩረት እምብዛም ነው። በዚህ መነሻነት ነርሶች በነርስ መመራት አለባቸው ተብሎ ነው÷ እሷ ወደ ኃላፊነት የመጣቸው። “እዚህ ስመጣ ነገሮች አስቸጋሪ ነበሩ። በነርሲንግ ብቻ ከአራት መቶ በላይ ሰራተኛ ነው ያለው። ይኼንን ስታፍ የሚያስተባብሩ ደግሞ ወደ 38 የዲፓርትመንት ኃላፊዎች አሉ።
በፊት የራሴ አለቃ ራሴ ነኝ። ሪፖርት ነበር በብዛት የማዘጋጀው። አሁን ደግሞ ለኔ ነው ሪፖርት የሚቀርብልኝ። በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት አስቸጋሪዎች ነበሩ። በዚያ ጊዜ ቤቱን ፈር ለማስያዝ የሰውነቴ ክብደት ሁሉ ቀንሷል” በእርግጥ ሲስተር ፂዮን ወደዚህ ኃላፊነት ከመጣች ጀምሮ በስሯ ካሉ ነርሶች አለባበስ ጀምሮ ብዙ ነገር ተለውጧል። ከሷ በታች ባሉ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ የስራ ኃላፊዎችንም በማብቃት ረገድ ብዙ ስራዎች ሰርታለች።
በማንኛውም ሰዓት በቦታዋ ቢተኩ ያለአንዳች መደነቃቀፍ ስራቸውን እንደሚወጡም በኩራት ትናገራለች። ከሲስተር ፂዮን ሙሉጌታ ጋር አብረው ከሚሰሩ ባለሙያዎች አንዷ ናት። ሲስተር ሊሊ ላምቤቦ። የሆስፒታሉ ቀዶ ህክምና ክፍል የነርሶች አስተባባሪ ናት። ስለ ሲስተር ፂዮን ይህንን ብላናለች፦ “በሲስተር ፂዮን ስር ሆኜ ነው የአስተባባሪነት ስራዬን የምሰራው። በቆይታዬ ከሷ በርካታ ተሞክሮዎችን ቀስሜያለሁ።
በተለይም የምትሰጠው አመራር መልካም ነው። ሰራተኛ ሁሉ አንድ አይደለም። በአግባቡ ስራውን የማይሰራ ሰው ሲያጋጥማት ከአስተባባሪው ጋር አስቀምጣ መጀመሪያ በምክር ነው ልትመልሰው የምትሞክረው። በሂደትም የምትወስደው እርምጃ ሌላውን ሰራተኛ ጭምር የሚያስተምር ነው” በነገራችን ላይ ሲስተር ፂዮን የትምህርቷን ነገር ዲፕሎማ ላይ አልተወችውም። “ዲፕሎማ የትም ይገኛል። በዚህ ስራ ይዣለሁ ብለሽ እንዳትዘናጊ” የሚለው የአባቷ ምክር ለተሻለ ነገር እንድትተጋ አድርጓታል። በትዳር ውስጥ ሆና ልጅ እያሳደገች ጭምር 2005 ዓ.ም ላይ በዲግሪ ተመርቃለች።
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የሰጣትን የትምህርት ዕድል ተጠቅማ የማስተርስ ዲግሪዋን ይዛለች። አሁን ደግሞ በተለይም የጀመረችውን የአመራርነት መንገድ ለማጠናከር እንዲረዳት በማሰብ በሊደርሺፕ ማኔጅመንት በግሏ ለሌላ ማስተርስ ዲግሪ በመማር ላይ ትገኛለች። ታታሪዋ ነርስ በትዳርም ስኬታማ ናት። ለስኬቷ ሁሉ አጋዥ ባል አላት። በትዳር ቆይታዋም ሁለት ልጆችን አፍርታለች።
ወሰኔ በበኩላቸው በዘንድሮው ዓመት በዞኑም ይሁን በከተማ አስተዳደሩ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ነው የተናገሩት፡፡ በቡናና በአርቲ ልማትም የተሰሩ ስራዎች በጠንካራ ጎን መገምገማቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ዞኑ የብዙ ገፀ-በረከቶች ባለቤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የመንገድ ግንባታን በተመለከተ ብዙ ተሽከርካሪዎች የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ በመሆኑ የተጓተቱ ግንባታዎች በለውጡ ማግስት ይፈታሉ የሚል እሳቤ እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡
አጋጣሚ ሆኖ መንገዱ በፍጥነት እየሄደ ባለበት ከዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ ተቋርጦ መቆየቱን ከንቲባው ጠቁመው፣ ይህንንም የከተማውም ይሁን የዞኑ መንግስት ከክልል እስከ ፌደራል ጉዳዩን ለመጨረስ ሲመላለሱ እንደነበር ነው ያስታወሱን፡፡ የመንገዱ ችግር ቢፈታ ዞኑ ብዙ ሀብቶችን ለማዕከላዊ፣ ለሀገር ውስጥና ለዓለም ገበያ ማቅረብ እንደሚችል ተናግረው፣ አስቀድሞ በመንገድ ስራው ብዙ ስርቆቶች እና ችግሮች እንደነበሩም አመልክተዋል፡፡
በዚህም ግንባታውን በቅርብ ቀን አስጀምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመጨረስ ዞኑን ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችልባቸውን ስራዎች ክፍት ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። ይህም ውጤት እንደሚያመጣ እምነታቸው እንደሆነ ከንቲባው አስረድተዋል።
More Stories
“እግሬ ተጎዳ እንጂ አእምሮዬ አልተጎዳም”
“በመጀመሪያዎቹ ደረጃ ላይ ያለው ካንሰር በህክምና የሚድን ነው” – ዶክተር እውነቱ ዘለቀ
መሥራት ችግርን የማሸነፊያ መንገድ ነው