የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በሠላማዊ መንገድ በመፍታት ሀሉም ለሠላም ዘብ መቆም እንዳለበት ተገለፀ
በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በኦቾሌ ላንተ ቀበሌ በኦርቶዶክስ እና በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መካካል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባትን ለመፍታት ዕርቀ ሠላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።
በዕርቀ ሠላም ኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የጋሞ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሀኪሜ አየለ፤ ኢትዮጵያ የተለያዩ ሀይማኖቶች በመቻቻል፣ በመከባበር፣ በመደጋገፍና በአንድነት የሚኖሩባት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል።
በመሆኑም ልዩነቶችን በማጥበብ በየአካባቢው የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በምክክር መፍታት የአካባቢውን ሠላም በማጽናት የብልፅግና ተምሳሌት ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በተለይም ዞኑ የሰላም ተምሳሌት በመሆኑ የአካባቢውን ሠላምና አንድነትን ለማይፈልጉ ፀረ ሠላም ኃይሎች በር ባለመክፈት የሚያግባቡ ጉዳዮችን በማጠናከር ለልማት እንዲተጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ዘይቴ በበኩላቸው፤ ሠላም የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ ዘላቂ ሠላምን በማምጣት ረገድ የሀይማኖት ተቋማት ሚናቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በዙሪያ ወረዳው በኦቾሎ ላንተ ቀበሌ በኦርቶዶክስ እና በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ዘንድ ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት ዕርቅ ሠላም በመፈፀሙ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
የሀይማኖት አባቶች በአካባቢው የመቻቻል፣ የመከባበር፣ የመደጋገፍ እና የፍቅር ዕሴቶች በህብረተሰቡ ዘንድ ለማጎልበት መስራት እንዳለባቸውም አቶ አለማየሁ አሳስበዋል።
እርቀ ሠላሙ ዘላቂ እንዲሆን የሀይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች የበኩላቸውን እንደሚወጡ በሰጡን አስተያየት አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፡ አለሚቱ አረጋ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ኦሞ እና በኣሪ ዞን ማህበረሰብ መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችን በማስወገድ በልማት እርስ በእርስ በማስተሳሰር ሰላምን ለማፅናት በአካባቢዉ የፖሊስ ፋዉንዴሽን ተቋቋመ
የሚዛን አማን ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በበጀት አመቱ ከማህበረሰቡ በመቀናጀት የከተማዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስከበር ከፍተኛ ስራ መስራቱን ገለጸ
ጽዱ ከተማ ለመፍጠር የህብረተሰብ ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገለፀ