በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ86 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ
በጎፋ ዞን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና በሁሉም ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ታምራት ይገዙ በሳውላ ከተማ ፈተናውን ባስጀመሩበት ወቅት ከኩረጃ ነጻ እና ደህንነቱን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ባለድርሻ አካላትና ተማሪዎች የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቆ በክልሉ ሁሉም የፈተና መስጫ ማዕከላት ከ86 ሺህ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እየወስዱ መሆንናቸውን ተናግረዋል።
ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀው ከኩረጃ ነጻ እና ደህንነቱን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ዶ/ር ታምራት ጠቅሰዋል፡፡
የጎፋ ዞን ትምሀርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሞገስ መኩሪያ እንደገለጹት፤ በዞኑ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 8 ሺህ 169 ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዞኑ በ228 ትምህርት ቤቶች 37 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስፈትኑ ሲሆን 70 ትምህርት ቤቶች በተመረጡ ክላስተር ማዕከላት እንዲሁም 11 ትምህርት ቤቶች ባሉበት ትምህርት ቤት ፈተና እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የሳውላ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያዕቆብ በተላ፤ በከተማው የዘንድሮው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በ17 ትምህርት ቤቶች ላይ 1 ሺህ 307 ተማሪዎች ፈተና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረው።
በዘንድሮው ፈተና ለአንዲት ተፈታኝ ተማሪ በወሊድ ምክንያት በሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ፈተና እየተሰጠ መሆኑን አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በከምባታ ዞን የሺንሽቾ ከተማ የመሠረተ ልማት ተግባራት በማጠናከር የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ
የተቀናጀ የመሬት አያያዝ ፖሊሲ የቡና ምርታማነትን እንደሚያሳድግ ተገለፀ
የቀርከሃ ምርትን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው ሊስሩ እንደሚገባ በኣሪ ዞን ዎባ ኣሪ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች ጠየቁ