በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተጀመረ
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በበካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ በሚገኘው ባርታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፈተናውን አስጀምረዋል።
በክልሉ 32 ሺህ 899 ተማሪዎች በ1 ሺህ 94 የመፈተኛ ጣቢዎች የሚፈተኑ ሲሆን፤ ከእነዚህም 15 ሺህ 590 ሴቶችና 17 ሺህ 309ኙ ወንዶች ናቸው።
በተመሳሳይ በካፋ ዞን ሁሉም ወረዳዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተጀመረ ሲሆን፤ 10 ሺህ 692 ተማሪዎች በ432 የመፈተኛ ጣቢያዎች ይፈተናሉ።
ፈተናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ይሰጣል።
ዘጋቢ፡ ትዕግስቱ ጴጥሮስ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ