ሀዋሳ፡ ሰኔ 09/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) እንደ ዞን በኮሮርማ ምርት ከ20 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት እየለማ መሆኑን በኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ የቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት አሰታወቀ።
በኣሪ ዞን ዎባ ኣሪ ወረዳ በሰፊው ከሚመረቱ በርካታ የምርት አይነቶች የኮረሪማ ምርት አንዱ ነው።
ለዚህም የኮረሪማ ምርትና ምርታማነትን በአርሶ አደሩ አከባቢ በማሳደግ ከምርቱ የሚያገኙትን ውጤት በተሻለ ዋጋ በመሸጥ ከህገ ወጥ ደላላ ለመቆጣጠር ምቹ የግብይት ማዕከል በመቋቋም እየሰራ መሆኑን የዎባ ኣሪ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈጠነ አየነው ገልጸዋል።
በዚህም የቁጥጥር ተግባር የምርቱ ውጤት ላይ የአርሶ አደሩ ትኩረት የተሻለ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው እንደ ወረዳ ሽፋኑ ከ7 ሺህ 650 በላይ መሆኑን አስረድተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጋናክሽ አርዳክ እንደገለጹት ለምርቱ የአየር ሁኔታው ምቹ በሆነባቸው አከባቢዎች አርሶ አደሩ በስፋት እያለሙና እያመረቱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ይህ የኮረሪማ ምርት በአርሶ አደሩ አከባቢ ለየት ያለ የገቢ ምንጭ አማራጭ በመሆኑ ለዘርፉ ውጤታማነት የግንዛቤ ሥራዎችን ጨምሮ በርካታ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው ሽፋኑ እንደ ዞን 20 ሺህ 218 ሄክታር መሬት እንደሆነም ተናግረዋል።
በኮረሪማ ምርት እያለሙ ምርቱን በተሻለ ዋጋ በመሸጥ ሕይታቸው ላይ በተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን የተናገሩት አርሶ አደር አምሳቸው ማናሌው እና አስቻለው ጌታቸው በዚህም የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ: ፍቃዱ ግዲ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
መሳላ የሕዝቦችን ትስስር፣ አንድነትና መከባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው – የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች
የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል ከብሔሩ ዘመን መለወጫነት ባሻገር የሚያበረክተው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ ነው – የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ”ያሆዴ” በዓልን ስናከብር ስለ ሀገራችን ልማትና ስለ ህዝባችን አብሮነት የበለጠ የምንተጋበት ወቅት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል