በጎፋ ዞን ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ክልላዊ የ6ኛ ክፍል ፈተና እየተሰጠ ነው
በጎፋ ዞን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና በሁሉም ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል፡፡
የጎፋ ዞን ትምሀርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሞገስ መኩሪያ እንደገለጹት፤ በዞኑ በ279 ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 12 ሺህ 596 ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
80 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስፈትኑ ሲሆን 184 ትምህርት ቤቶች በተመረጡ ክላስተር ማዕከላት እንዲሁም 15 ትምህርት ቤቶች ባሉበት ትምህርት ቤት ፈተና እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ፈተናውን በተቀናጀ መንገድ ለመስጠት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀው፤ ከኩረጃ ነጻ እና ደህንነቱን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡
የሳውላ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያዕቆብ በተላ፤ የዘንድሮው የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በ17 ትምህርት ቤቶች ላይ1 ሺህ 897 ተማሪዎች 67 የፈተና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ተናግረው የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቆ ፈተና መሰጠት መጀመሩን ገልጸዋል።
የሚሰጠው ምዘና ከኩረጃ ነጻ ለማድረግ በትኩረት መሰራቱን አብርተዋል።
የሳውላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በላይነህ ባህሩ ክልላዊ የ6ኛ ክፍል ፈተና ዓመቱን ሙሉ በቂ ዝግጅት የተደረገበትና ተማሪዎችና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በሰላማዊ ሁኔታ ፈተና መስጠት መጀመሩን አብራርተዋል።
በስፍራው የተገኙ የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳርና ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ምናሴ ኤልያሰ፤ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንሰተው ፈተናው በዞኑ ባሉ የፈተና መስጫዎች በሰላማዊ ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑን ገልጽዋል።
በመጨረሻም ለሁሉም ተፈታኞች ስኬታማ እና ውጤታማ ፈተና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች በመመለስ በኩል ከመንግስት ጥረት ባለፈ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና የጎላ መሆኑን የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ተናገሩ
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን አስጀመሩ
በኢራን ጦርነት ማክተም ላይ የተደረሰው ጊዜያዊ ስምምነት የአክሲዮን ገበያዎችን ሲያንረው ለነዳጅ ዋጋ መቀነስ ግን ምክንያት ሆኗል