ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን አስጀመሩ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 08/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን በወልቂጤ ከተማ በያበሩስ 2ኛ ደረጃ ትምህር ቤት አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በማዕከሉ የፈተና አሰጣጥ ሂደት ምን እንደሚመስል በየክፍሉ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ መፈተን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በክልሉ 91 ሺህ 918 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ ተጠቁሟል።
የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናው ዛሬ እና ነገ የሚሰጥ ሲሆን በቀጣይ ቀናቶች በክልሉ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማን ጨምሮ ሌሎችም የክልሉ፣ የዞኑና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሌሎችም ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ እርካብነሽ ወ/ማርቆስ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
መሳላ የሕዝቦችን ትስስር፣ አንድነትና መከባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው – የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች
የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል ከብሔሩ ዘመን መለወጫነት ባሻገር የሚያበረክተው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ ነው – የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ”ያሆዴ” በዓልን ስናከብር ስለ ሀገራችን ልማትና ስለ ህዝባችን አብሮነት የበለጠ የምንተጋበት ወቅት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል