የአይቮሪኮስት የወደፊት ተስፋ
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የ2026 ዓለም ዋንጫ፣ የአይቮሪኮስት ብሄራዊ ቡድን ድንቅ ወጣት አማድ ዲያሎ በታሪክ መዝገብ ውስጥ ስሙን አስፍሯል።
አማድ ዲያሎ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ዝሆኖቹ ኢኳዶርን 1ለ0 ባሸነፉበት ጨዋታ ጎል በማስቆጠር፣ ለሀገሩ ብሄራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ መድረክ ጎል ያስቆጠረ በእድሜ ትንሹ ተጫዋች መሆን ችሏል።
በ23 ዓመት ከጥቂት ወራት እድሜው ይህንን ስኬት የተጎናጸፈው አማድ፣ ለአይቮሪኮስት እግር ኳስ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ድንቅ ወጣት ተጫዋች መሆኑን አሳይቷል።
አማድ ዲያሎ በዓለም ዋንጫ መድረክ የሀገሩን መለያ ለብሶ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሯል።
በ23 አመቱ ይህንን ስኬት በማሳካት፣ ከዚህ ቀደም የነበሩ ታላላቅ የአይቮሪኮስት ኮከቦችን በመቅደም፣ በዓለም ዋንጫ ለሀገሩ ጎል ያስቆጠረ ትንሹ ተጫዋች ሆኗል።
ወጣቱ ኮከብ በጨዋታው ተቀይሮ ከገባ በኋላ በሜዳ ላይ የነበረው እንቅስቃሴ፣ በኳስ ቁጥጥር፣ በፈጠራ ብቃቱ እና ጎል ለማስቆጠር ባሳየው የማጥቃት ፍላጎት የቡድኑን የማጥቃት መስመር በእጅጉ አሳድጎታል።
ይህ ስኬት ለአይቮሪኮስት ብቻ ሳይሆን፣ ለአፍሪካ እግር ኳስ የወደፊት ተስፋ ትልቅ ማሳያ ነው።
አማድ ዲያሎ በቀጣይ ጨዋታዎች ምን ያህል ርቀት ሊሄድ እንደሚችል አድናቂዎቹ በጉጉት እየጠበቁት ነው።
አማድ ዲያሎ የትውልዱ ድምጽ ሆኖ፣ በታላቁ መድረክ ላይ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል።
ይህ ጎል የአንድ ትልቅ ኮከብ መፈጠር ማሳያ እንደሆነ የሚስማሙበት አድናቂዎች፣ ተጫዋቹ ለቀጣዩ የአይቮሪኮስት የዓለም ዋንጫ ጉዞ ቁልፍ ተጫዋች እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የላቸውም።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ኬፕ ቨርዴ በታላቁ መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ
የዓለም ዋንጫውን የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት በቁጥጥሯ ስር ያዋለችው ጀርመን
ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ የሊጉ ሻምፒዮን ለመሆን በእጅጉ ተቃረበ