የ2026 የዓለም ዋንጫ፡ የዛሬው የውድድር መርሐግብሮች
ዛሬ ሰኔ 6 ቀን 2026 ዓ.ም የዓለም ዋንጫው በከፍተኛ ፉክክር ቀጥሎ ሲውል በአስራ አንድ ሰዓታት ውስጥ የሚከናወኑ አራት ተጠባቂ ጨዋታዎች የዕለቱን ድባብ ይቆጣጠራሉ።
ብራዚል ከ ሞሮኮ፡ የአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የመጀመሪያው ፈተና
የዓለም ዋንጫው ስኬታማዋ ብራዚል፣ በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ስር አዲስ ምዕራፍ ጀምራለች።
በቡድኑ ውስጥ እንደ ቪንሰስ ጁኒየር፣ ራፊንሀ እና ኔይማር ያሉ ኮከቦች ቢኖሩም፣ ኔይማር በጉዳት ምክንያት የዛሬውን ጨዋታ እንደሚያመልጠው ተረጋግጧል።
በሌላ በኩል ባለፈው የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ የነበረችው ሞሮኮ ጠንካራ ስብስቧን በመያዝ ለብራዚል ጠንካራ ፈተና እንደምትሆን ይጠበቃል።
ይህ ተጠባቂ ጨዋታ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
ስኮትላንድ vs ሀይቲ፡ የረጅም ጊዜ ጥበቃ ፍፃሜ
ከ28 ዓመታት ረጅም የጥበቃ ጊዜ በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫ የተመለሰችው ስኮትላንድ፣ ሀይቲን ትገጥማለች።
የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች የሆነው እና የሴርያ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ማክ ቶሚናይ፣ በሆድ ህመም ምክንያት በዛሬው ጨዋታ ላይ መሰለፉ አጠራጣሪ መሆኑ ስኮትላንዳውያንን አሳስቧል።
ጨዋታው ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ መካሄድ ይጀምራል።
በሌሎች ጨዋታዎች የዕለቱ መክፈቻ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት የ2022ቱ ዓለም አስተናጋጇ ኳታር ከስዊዘርላንድ ጋር የምታደርገው ትንቅንቅ ሲሆን የዕለቱን ውሎ አውስትራሊያ እና ቱርክ ነገ ከማለዳው 1 ሰዓት ላይ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል በሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ይቋጫል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዝርፊያ ተፈፀመበት
ማንቸስተር ዩናይትድ ማቲየስ ፈርናንዴዝን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው
የሞት ጥላን የተሻገረው ራውል ሂሜኔዝ