ማንቸስተር ዩናይትድ ማቲየስ ፈርናንዴዝን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው
ማንቸስተር ዩናይትድ የዌስትሃም ዩናይትድን ወጣት አማካይ ማቲየስ ፈርናንዴዝን ለማስፈረም የመጀመሪያ የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑ ተዘግቧል።
ዌስትሃም ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ተከትሎ የ21 ዓመቱ አማካይ ከክለቡ ለመልቀቅ በከፍተኛ ግምት ውስጥ መግባቱ ተሰምቷል።
የዩናይትድ የአሰልጣኝ ቡድን ፈርናንዴዝን የአማካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር እንደ ቁልፍ ተጫዋች ይመለከቱታል። በተለይም ካሴሚሮ ክለቡን በነፃ ዝውውር መልቀቁን ተከትሎ ቡድኑ በዚያ ቦታ ላይ ክፍተት ተፈጥሮበታል።
ዌስትሃም ተጫዋቹን ለመልቀቅ 80 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ዋጋ ቢጠይቁም ማንቸስተር ዩናይትድ ይህንን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ለመክፈል ፈቃደኛ እንዳይደለ ስካይ ስፖርት አስነብቧል።
ሁለቱ ክለቦች ስምምነት ላይ ለመድረስ ድርድር እንደሚያስፈልጋቸው ይጠበቃል።
መዶሻዎቹ ፈርናንዴዝን ባለፈው ክረምት ከሳውዝሃምፕተን ያስፈረሙት በ38 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር።
ማቲየስ ፈርናንዴዝ ባለፈው የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ካሉ ምርጥ ወጣት ተጫዋቾች አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል።
የዌስትሃም የውሳኔ ሰጪ አካላት፣ ተጫዋቹ ለቀድሞው የክለቡ ኮከብ ዴክላን ራይስ (በ2023 ወደ አርሰናል በ105 ሚሊዮን ፓውንድ የተሸጠው) እኩል ብቃት የመድረስ አቅም እንዳለው ያምናሉ።
በሊጉ ውስጥ ካሉ ጠንካራ የተከላካይ አማካዮች አንዱ ነው።
ከፍተኛ ርቀት በመሮጥ እና ኳስ በማሳደድ የሚታወቅ ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ አማካዮች መካከል ብዙ ርቀት በማካለል ከምርጥ አስሩ ውስጥ ይካተታል።
እንደ 6 ቁጥር እና 8 ቁጥር ተጫዋች በመሆን በሁለቱም ሚናዎች የመጫወት አቅም አለው።
ዌስትሃም ለሚቀጥለው የውድድር ዘመን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለመመለስ በሚያደርጉት ጥረት ፈርናንዴዝን በቡድኑ ውስጥ ማቆየት ቢፈልጉም የገንዘብ ችግር እና የተጫዋቹ ከፍተኛ ፍላጎት ዝውውሩን የማይቀር አድርጎታል።
ከአርሰናል እና ፒኤስጂ ጋር ስሙ በስፋት እየተነሳ ቢገኝም ማንቸስተር ዩናይትድ ግን ዝውውሩን ለመጨረስ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው።
ዩናይትድ በዚህ ክረምት ኤደርሰንን ከታላንታ ያስፈረመ ቢሆንም ፈርናንዴዝን በመጨመር በአዲሱ የውድድር ዘመን የጠንካራ አማካይ ክፍል ባለቤት ለመሆን ይፈልጋል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዝርፊያ ተፈፀመበት
የ2026 የዓለም ዋንጫ፡ የዛሬው የውድድር መርሐግብሮች
የሞት ጥላን የተሻገረው ራውል ሂሜኔዝ