የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሣይንስ፣ የፈጠራ ስራዎች ውድድርና አውደ ርዕይ መካሄድ ጀመረ
ሀዋሳ: ሰኔ 05/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ 3ኛውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሣይንስ፣ የፈጠራ ስራዎች ውድድርና አውደ ርዕይ በይፋ አስጀምረዋል።
“ማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን የሣይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማዕከል እናድርግ” በሚል መሪ ቃል ለ3ኛ ጊዜ በቡታጅራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶክተር ባይሳ በዳዳ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ አየለች እሸቴ የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም የሳይንስ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ፣ የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተር ፕራይዝ ልማት ቢሮ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
በአውደ ርዕዩ ልዩ ልዩ የፈጠራ ስራዎች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተመላክቷል።
3ኛው የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ውድድር አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ የሳይንስ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ፣ የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተር ፕራይዝ ልማት ቢሮ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ በጋራ ማዘጋጀታቸው ተመልክቷል።
ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ

More Stories
“አንድነት የሚገነባው በውይይት ነው፤ ሰላም የሚጠናከረው በመግባባት ነው” ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ሼክ አህመድ ቡርሃን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት
መደበኛ ባልሆነ መልኩ የሎተሪ ዕድል ሙከራን “ዕቁብ” በሚል ሽፋን በህገ-ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት አሳሰበ
መንግስት ባለፉት ጊዜያት በስርዓተ ትምህርት እና በመማር ማስተማር ሂደት የነበረውን ክፍተት ለመሙላት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጥናትና ምርምር የተደገፈ ስራ በመስራት መደገፍ እንደአለባቸው ተገለጸ