ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የዲላ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ከፈቱ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 04/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የዲላ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ከፍተዋል፡፡
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በብቃት ለመፍታትና የዜጎችን እንግልት መቀነስ የሚያስችለው የመሶብ አገልግሎት ነው ተመርቆ ለስራ ክፍት የሆነው።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 3ኛ የሆነውን የዲላ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ባጭር ጊዜ ውስጥ በብቃት በማጠናቀቅ ርዕሰ መስተዳድሩ በይፋ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገውታል፡፡
ማዕከሉ 4 የፌዴራል እና 5 የክልል ተቋማት አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር በማጣመር፤ 32 የተለያዩ አገልግሎቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በታገዘ፤ በተቀላጠፈ ዘመናዊ አሰራር በመስጠት ሥራ የሚጀመር ይሆናል።
መሶብ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በተቀላጠፈ ዘመናዊ አሰራር በቀላሉ የተለያዩ የክልል እና የፌዴራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል አላስፈላጊ ቢሮክራሲን የሚያስቀርና ጊዜና ወጪ ቆጣቢ ኢኒሼቲቭ ነው።
ዘጋቢ፡ ባዬ በልስቲ

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው