የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር እንዲኖር የተለያዩ ፕሮጀክቶች መዘጋጀታቸው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 02/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር እንዲኖር የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተዘጋጅቶ እየተሰራ መሆኑን የኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስተር አስታወቀ፡፡
በናቡ ኢትዮጵያና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ አማካኝነት በካፋ ዞንና በቤንች ሸኮ ዞን በሚገኙ የውሃ አካላት ዳሰሳ ጥናቶች ዙሪያ በቦንጋ ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
በኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሃይድሮሎጂና ውሃ ጥራት ዴስክ አስተባባሪ አቶ ይርጋዓለም እሱነህ ኢትዮጵያ በከርሰ-ምድርና ገጽ-ምድር የውሃ ሀብት የታደለች ሀገር መሆኗን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ በተለያዩ የሰው-ሰራሸና ተፈጥሮዊ ምክንያቶች እየተመናመነ እንደሚገኝ ነው አቶ ይርጋዓለም የተናገሩት፡፡
ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሀገሪቱን ውሃ ሀብት የመጠበቅ፣ የመንከባከብ እና የማልማት ስራ ትኩረት ሰጥቶ እያከናወነ ይገኛል ያሉት አቶ ይርጋዓለም፥ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር እንዲኖር ፕሮጀክቶች ተቀርጾ እየተሰራ ነው ብለዋል ፡፡
በፈዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የስርዓተ ምድር አጠቃቀምና ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ተሬሳ ጨመዳ በበኩላቸው፥ ውሃ አዘል መሬቶች እንዲያገግሙ የሚያስችል ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሀገሪቱ ከ9 ሺህ ሄክታር በላይ ውሃ አዘል መሬቶች እየተመናመነ መሆኑን በዳሰሳ ጥናት መረጋገጡን የገለጹት አቶ ተሬሳ፥ ከነዚህም ውስጥ 382ቱ ውሃ አዘል መሬቶች ጥበቃ እየተደረጋለቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲቻል በየደረጃው የሚገኙ አካላት ሚናቸውን የጎላ በመሆኑ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ብዙአየሁ ጫካ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው