በጠምባሮ ልዩ ወረዳ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያ ሆኖ መጠናቀቁን ተከትሎ የምስጋናና የዕውቅና መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ደጀኔ ለዕመንቾ እንደገለጹት፤ ህዝብ ሲተባበርና ሲደጋገፍ እንዲሁም የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ከፈጠረ የተሻለ ውጤት ይመዘገባል።
ለዚህም የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቁ የህዝቡን አንድነትና አብሮነት አመላካች ነው ብለዋል አቶ ደጀኔ።
የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ፤ የሀገር መጪውን ዕድል የሚወስን ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን ገልፀው ምርጫው ህብረተሰቡ ዲሞክራሲያዊ መብቱን እንዲያረጋግጥ ያስችላል ብለዋል።
የእለቱ የክብር እንግዳ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ እንደገለጹት፤ ህዝቡ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ የክልል፣ የልዩ ወረዳው እና የሙዱላ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና የቀበሌ ካቢኔ አባላት ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ: ጡሚሶ ዳንኤል – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው