ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የአርባምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከልን መርቀው ከፈቱ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 02/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሁለተኛው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአርባምንጭ ከተማ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ፈጣንና ከሙስና የፀዳ፣ ዜጎችን የሚመጥን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ኢንሼቲቭ ነው።
ዜጎች በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ወይም ከሥራ ቦታቸው ሆነው በዲጂታል ስርዓት እንዲያከናውኑ የሚያስችል ነው።
የአርባምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል ውስጥ 4 የፌደራል 5 የክልል ተቋማት በውስጡ የያዘ ሲሆን በአጠቃላይ 32 የተለያዩ የአገልግሎት አይነቶችን ይሰጣል።
የማዕከሉ ግንባታ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የተከወነ ሲሆን፣ የማማከር ስራውን ደግሞ የደቡብ ዲዛይናን ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ሀላፊነቱን ወስዶ አጠናቋል።
ዘጋቢ: ባዬ በልስቲ

More Stories
የጉራጌ ማህበረሰብ ባህላዊ እሴቶች ሳይበረዙ ለትውልድ ለማስተላለፍ የኪነ ጥበብ ዘርፉን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት 67 ቢሊየን ብር በጀት አጸደቀ
“እየተከልን ያለነው ችግኝ ብቻ ሳይሆን የምግብ ሉዓላዊነታችንን ጭምር ነው” – የኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር)