በሃይለማሪያምና ሮማን ፋዉንደሽን 297 ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ወደ ሥራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን የወረዳው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ገለጸ
ሀዋሳ፡ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኦሞ ዞን ሣላማጎ ወረዳ በሃይለማሪያምና ሮማን ፋዉንደሽን ለተደረጁ ማህበራት የፍዬልና የበሬ ስርጭት በማድረግ ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን የወረዳው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታዬሁ ምንባሌ ገለጹ።
ሃይለማሪያምና ሮማን ፋዉንዴሽን በወረዳው በ7 ነባር ቀበሌና በ3 አዲስ ቀበሌ በድምሩ 10 ቀበሌዎች ላይ 297 ኢንተርፕራይዝ ማህበራት ማደራጀታቸውን ጠቁመው፥ በበሬ ድለባ 64 ኢንተርፕራይዝ፣ በፍየል ማሞከት 27 ኢንተርፕራይዝ በደምሩ 91 ኢንተርፕራይዞች ሥራቸውን ሲጀምሩ ቀሪ 110 ኢንተርፕራይዞች በገሮና ሃና ክላስተርም ስርጭት እየተደረገ መሆኑን አቶ ስንታየሁ ተናግረዋል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህጉ ቅጣቱ እንዳሉት ሃይለማሪያምና ሮማን ፍዉንደሽን የአመለካከት ለውጥ ላይ የሰራዉ ስራ ከሁሉ ፕሮጀክት ለየት ያደርገዋል ስሉ ተናግረዋል።
አክለውም መንግስት የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለተግባሩ ስኬት በቅርበት ማህበራቱን እንዲደግፉና እንዲከታተሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ስርጭት የተደረገላቸው ወጣቶችም በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውንና ሰርተውም ራሳቸውን ለመለወጥ እንደሚተጉ አመላክተዋል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህጉ ቅጣቱ፥ የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጳሽማ ወሊክሮ፣ የሃይለማሪያምና ሮማን ፋውንደሽን የጂንካ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ አለማዬሁ እና የፕሮጀክቱ ማናጅመንት አካላትና የወረዳ ባለድርሻ አካላት በጋራ ስርጭት አካሂደዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
በሃይለማሪያምና ሮማን ፋዉንደሽን 297 ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ወደ ሥራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን የወረዳው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ገለጸ

More Stories
2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል
የጋሞ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የምርጫ ካርድ የመጣል ሂደት መጠናቀቁን ተከትሎ መግለጫ ሰጡ
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም ለመጠናቀቁ የመላው የክልሉ ህዝብ ተሳትፎ ላቅ ያለ ድርሻ ማበርከቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋር ምክር ቤት ገለፀ