ወጣቶች በሀገርና በሀገረ መንግስት ግንባታ በመሳተፍ ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር መግለጽ እንዳለባቸው በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ ወጣቶች ገለጹ
ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ የፈጠነች፣ በማኅበራዊ መስክ የበለጸገችና በፖለቲካዊ ምኅዳር የጎለመሰች “ተምሳሌት ሀገር” የማድረግ ታላቅ ራዕይ በወጣቱ ትከሻ ላይ ያረፈ ነው።
ይህ ራዕይ ከቃል ባለፈ ወደ ተግባር የሚቀየረው ወጣቶች በየአካባቢያቸው ለሚያጋጥሙ ችግሮች አዎንታዊ ምላሽ ሲሰጡ፣ በልማትና በሰላም ግንባታ ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ ሲያደርጉ እንደሆነም ወጣቶቹ ገልፀዋል።
ወጣቶች በሀገርና በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ ያላቸው ሚና የሚያቀራርቡ እና የሚያግባቡ ሀገራዊ ገዥ ትርክቶችን መከተል እንዳለባቸው ያነጋገርናቸው ወጣቶች ተናግረዋል።
ወጣት ልደታ ወልደ ስላሴ፣ወጣት ታምሩ ጎማ፣ ወጣት ስንታየሁ ከበደ እና ወጣት ናትናኤል ግርማ የቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ በወጣቱ መካከል ጠንካራ ትስስር እንዲፈጠር በማስቻል የተባበረች ሉአላዊ ሀገር ለመገንባት፣ ባለፉት አመታት ሰው ተኮር እና መሰራት ያለባቸው የልማት ስራዎች በየዘርፉ ሲከናወኑ እንደቆየም ገልፀዋል።
ወጣቶች አካባቢያቸውን ማወቅና በማንኛውም ሁኔታ ተስፋ ባለመቁረጥ ወደፊት መጓዝ እንዳለባቸውም ጠቁመው፥ መልካምና መጥፎ ነገርን በመለየት በራሳቸው ለመቆም ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ምክራቸውን ሰጥተዋል።
በቀጣይ አመታትም በሀገርና በሀገረ መንግስት ግንባታ በመሳተፍ ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር መግለፅ አለባቸው ያሉት ወጣቶቹ ማህበራዊ ሚዲያን ለሰላም ግንባታ መጠቀም ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በሀገራችን ብሎም በዞናችን በሁሉም ዘርፎች እየታዩ ያሉ ለውጦች አበረታች መሆናቸውን አንስተው ለዚህም መንግስት ለወጣቱ ተጠቃሚነት የሰጠው ትኩረት አንዱ ማሳያ እንደሆነ አመለክተዋል።
የሚቀራረቡና የሚያግባቡ ገዢ ትርክቶችን በመከተልና በማስረጽ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ወጣቶቹ ተናግረዋል።
ዘጋቢ: በተመስገን ዳጉሳ – ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የተማዎችን ውጤት ለማሻሻል በተደረገው ጥረት የተሻለ ውጤት እንደሚጠበቅ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለፀ
በሃይለማሪያምና ሮማን ፋዉንደሽን 297 ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ወደ ሥራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን የወረዳው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ገለጸ
2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል