ምርጫው ነጻ ፍትሀዊ እና ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን ተፈሪ የምርጫ ክልል የሚገኙ የሲቪክ ማህበራትና የፖለቲካ ፓርቲ ታዛቢዎች ተናገሩ
የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ እና የሲቪክ ማህበራት ፓርቲ ታዛቢዎች መካከል ወይዘሮ አጥናፏ ምትኩ ከኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽን ተወካይ ታዛቢ እና አቶ ዳዊት ዳኜ ከብልጽግና ፓርቲ ተወካይ ታዛቢ እንዲሁም አቶ ጌታሁን ሀይሉ ትብብር ኢትዮጵያ ለአንድነት ፓርቲ ተወካይ ታዛቢ፤ የዘንድሮ ምርጫው ከበፊቱ ለየት የሚያደርገው ከማለዳው አስራ ሁለት ሰአት እስከ ምሽቱ ስድስት ሰአት ህብረተሰቡ በትእግስት ተረጋግቶ ሲመርጥ መታዘብ መቻላቸውን ተናግረዋል።
በምርጫ ሂደቱም ይሁን በቆጠራው ወቅት ያለማንም ጣልቃ ገብነት ምርጫ አስፈጻሚዎች ተግባራቸውን በተገቢው መወጣታቸውን ጠቁመው፤ ከድምጽ አሰጣጡ በኋላ ቆጠራው ተደርጎ ጊዚያዊ ውጤት በተገቢው መለጠፉን መመልከት ችለናል ብለዋል።
በዚህም ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረበ ቅሬታ አለመኖሩን የተናገሩት ታዛቢዎቹ፤ ምርጫው በሰላም ያለምንም የጸጥታ ችግር መጠናቀቁን መታዘብ መቻላቸውንም ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አብዮት በቀለ – ከሚዛን ቅርንጫፍ

More Stories
“አንድነት የሚገነባው በውይይት ነው፤ ሰላም የሚጠናከረው በመግባባት ነው” ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ሼክ አህመድ ቡርሃን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት
መደበኛ ባልሆነ መልኩ የሎተሪ ዕድል ሙከራን “ዕቁብ” በሚል ሽፋን በህገ-ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት አሳሰበ
መንግስት ባለፉት ጊዜያት በስርዓተ ትምህርት እና በመማር ማስተማር ሂደት የነበረውን ክፍተት ለመሙላት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጥናትና ምርምር የተደገፈ ስራ በመስራት መደገፍ እንደአለባቸው ተገለጸ