የሀገሪቱ የነገ “ዕጣ ፈንታ” የሚወሰነው በምርጫ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚፈልጉት ፓርቲ ድምፃቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውንም አረጋግጠዋል።
7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ በአርባምንጭ ከተማ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን መታዘብ ችለናል።
የሀገሪቱ የነገ “ዕጣ ፈንታ” የሚወሰነው በምርጫ በመሆኑ ለሀገሪቱ ሰላም፣ ኢኮኖሚ እና ዴሞክራሲ የሚበጃቸውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የከተማው ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።
ምርጫው ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ከራሱ የሚጠበቀውን ሚና መወጣት እንዳለበት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡ ሰለሞን አላሶ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ
የአንድን ሀገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ትምህርትና ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ብቁ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት መስራት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)