መብታችንን ተጠቅመን ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል – በሸካ ዞን የአንድራቻ ወረዳ ነዋሪዎች
የምርጫ ካርዳቸውን ተጠቅመው ድምጽ ለመስጠት ነገን እየጠበቁ መሆኑን በሸካ ዞን የአንድራቻ ወረዳ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ነዋሪነታቸውን ካደረጉ አስተያየት ሰጪዎች መካከል አቶ መልካሙ አንደሞ እና አንድነት ሸሎ፤ የምርጫ ካርዳቸውን አስቀድመው ማውጣታቸውን እና ነገ ግንቦት 24ን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ለሀገር እድገት ይጠቀማል የሚሉትን ፓርቲ በመምረጥ መብታቸውን ለመጠቀም የምርጫውን ቀን በመጠባበቅ ላይ መኾናቸውን አንስተዋል።
ዜጎች የምርጫ ካርዳቸውን መጠቀም አለባቸው ያሉት ደግሞ የሼራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ፍሬህይወት ካሮ እና የገቲባ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ከበደ ደስታ እንዲሁም ወጣት አሳምነው ታዬ ናቸው።
ከሁሉም ነገር ለሀገር ሠላም ቅድሚያ መስጠት ይገባል ያሉት ነዋሪዎቹ፤ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።
ምርጫው ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: ታሪኩ ታደሰ – ከማሻ ጣቢያችን
መብታችንን ተጠቅመን ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል – በሸካ ዞን የአንድራቻ ወረዳ ነዋሪዎች

More Stories
አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ
የአንድን ሀገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ትምህርትና ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ብቁ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት መስራት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)