“ኢትዮጵያ ትመርጣለች!”
ግንቦት 24 ለሚካሄደው ምርጫ የምርጫ ቁሳቁሶች በተገቢው መንገድ እየተሰራጩ መሆናቸውን የቢጣ ጌሻ ምርጫ ክልል አስተባባሪ ገለጹ
የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ አቶ ኢዮብ አሰፋ፤ በምርጫ ክልሉ በአጠቃላይ 110 የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የቢጣ ጌሻ ምርጫ ክልል በቢጣ፣ ጌሻና ከፍል ሳይለም ወረዳዎችን እንደሚያጠቃልል ገልጸዋል።
በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶች የማሰራጨት ስራ በስኬት እየተከናወነ ነው ብለዋል።
በደካ ከተማ አስተዳደር የአደባባይ ምርጫ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ቢንያም ብርሃኑ እና የጤና ጣቢያ ሰፈር ምርጫ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ምስጋናው ሀይሌ ለምርጫ ማስፈጸሚያ የተላኩ ቁሳቁሶችን መረከባቸውን ተናግረዋል።
ቁሳቁሶቹ ደህንነታቸው በተጠበቀ ቦታ ላይ መቀመጣቸውን የጠቆሙቶ የጣቢያዎቹ ኃላፊዎቹ፤ ለድምፅ መስጫው ዕለት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ ሀብታሙ ታደሰ

More Stories
አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ
የአንድን ሀገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ትምህርትና ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ብቁ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት መስራት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)