በስልጤ ዞን ላንፉሮ ምርጫ ክልል የቅድመ ምርጫ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል
የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት መጠናቀቁን
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የላንፉሮ ምርጫ ክልል ሀላፊ አቶ ኑረዲን በርጫ ገልፀዋል።
7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ ለማድረግ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የተናገሩት አቶ ኑረዲን፤ በምርጫ ክልሉ 70 ሺህ 258 መራጮች ድምፃቸውን ለመስጠት መመዝገባቸውን ገልፀዋል።
በላንፉሮ ምርጫ ክልል በሚገኙ በሶስቱም ማለትም በሚቶ ወረዳ 25 ፣ በጦራ ከተማ አስተዳደር 16 እንዲሁም በላንፉሮ ወረዳ ደግሞ 36 ምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን በድምሩ 77 ምርጫ ጣቢያዎች እንዲሁም 3 ንዑስ ምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ ሲሉ ጠቁመዋል።
ኃላፊው በምርጫ በጣቢያዎቹ የቁሳቁስ ስርጭቶች መደረጋቸውን አስታውቀዋል።
ዘጋቢ፡ አለምሸት ግርማ

More Stories
አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ
የአንድን ሀገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ትምህርትና ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ብቁ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት መስራት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)