በእጃችን ያለው የምርጫ ካርድ እንዳይባክን የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ
ለ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ነገን ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሻግር መንግሥት ለመምረጥ ዕለቱን በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸውን ከይርጋጨፌ ነዋሪዎች አቶ አክሊሉ መኩሪያ፣ ወ/ሮ የኔነሽ ባሬ እና ሌሎችም ተናግረዋል፡፡
የወሰዱትን የምርጫ ካርድ በጥንቃቄ በማስቀመጥ በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ዴሞክራሲያዊ መብት በመጠቀም ለሚያምኑት ፓርቲ ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡
በእጃችን ያለው የምርጫ ካርድ ለቀጣይ ብሩህ ተስፋ ወሳኝ መሆኑን በመረዳት እንዳይባክን ጥንቃቄ በማድረግ የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
በእጃችን ያለው የምርጫ ካርድ እንዳይባክን የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ

More Stories
አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ
የአንድን ሀገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ትምህርትና ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ብቁ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት መስራት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)