በአንገጫ ቁጥር 1 የምርጫ ክልል ለምርጫ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች እየተሰራጩ መሆኑ ተገለፀ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አንገጫ ቁጥር 1 የምርጫ ክልል ቁሳቁሶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጩ ይገኛል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አንገጫ ቁጥር 1 የምርጫ ክልል ኃላፊ አቶ ሰላሙ ማርቆስ፤ በምርጫ ክልሉ 61 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።
በየምርጫ ጣቢያው በትላንትናው እለት 53 የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሰራጩ ገልጸው፤ 10 የምርጫ ጣቢያዎች አሁን እያሰራጩ መሆኑን ነው የገለጹት።
አቶ ሰላሙ እንደተናገሩት፤ ነገ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ አንገጫ ቁጥር 1 ምርጫ ክልል 50 ሺህ 3 መቶ 11 ድምጽ ለመስጠት መራጮች እንደተመዘገቡ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ: ሐና በቀለ

More Stories
አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ
የአንድን ሀገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ትምህርትና ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ብቁ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት መስራት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)