“ድምጽ ለመስጠት ተዘጋጅተናል” – የቢጣ ገነት ከተማ ነዋሪዎች
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት ይካሄዳል፡፡
ጣቢያችን በቢጣ ጌሻ ምርጫ ክልል ቢጣ-ገነት ከተማ ተገኝቶ የከተማዋን ነዋሪዎች አነጋግሯል፡፡
ካነጋገርናቸው ነዋሪዎች መካከል አቶ ተረፈ ከበደ፣ አቶ ሙሉጌታ ዘውዴ፣ ወይዘሮ አለሚቱ ሃይሌ፣ ወጣት ምንላርግህ ቆጭቶ እና ወጣት ዘውዲቱ አምቦ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት አጠናቀው ቀኑን እየጠበቁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ይበጀናል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን ካርድ በመውሰድ ቀኑን በጉጉት በመጠበቅ ላይ እንገኛለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ከምርጫው ጎን ለጎን የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ እንደሚገባም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ዳንኤል መኩሪያ

More Stories
አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ
የአንድን ሀገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ትምህርትና ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ብቁ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት መስራት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)