በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ወደየምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ መሆኑ ተገለጸ
ግንቦት 24/2018 ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ የማሰራጨቱን ስራ እያጠናቀቀ መሆኑን የምርጫ ክልሉ አስተባባሪው ተናግረዋል።
በመሎ ኮዛ ምርጫ ክልል መደበኛ 84 የምርጫ ጣቢያዎች እና 2 ንዑስ እንዲሁም 6 ሀገር አቀፍ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚፎካከሩባቸው የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ መሆኑን የምርጫ ክልሉ አስተባባሪው ተናግረዋል።
የመሎ ኮዛ ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ አራታ በተላ፤ እስካሁን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው የምርጫ ቁሳቁስ ወደየምርጫ ጣቢያዎች ስርጭት መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
ቀሪውን የቁሳቁስ ስርጭት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
የፀጥታ አካላት ከፀጥታና ደህንነት ጥበቃ በተጨማሪ በቁሳቁስ ስርጭት ወቅት አስፈላጊውን እጀባ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡ ድጋፌ ድክሬ – ከሳውላ ጣቢያችን
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ወደየምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ መሆኑ ተገለጸ

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)