ለድምጻችን ዋጋ በመስጠት ነገ በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚበጀንን ለመምረጥ ተዘጋጅተናል – የቢይራሌ ከተማ ነዋሪዎች
ሀዋሳ: 23/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለድምጻችን ዋጋ በመስጠት ነገ በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚበጀንን ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ በደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ የቢይራሌ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
በወረዳው ቢራይሌ ከተማ የደቡብ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋዜጠኞች ጋር ቆይታ ያደረጉት አስተያየት ሰጪዎች እንደገለፁት፥ ሰኞ ግንቦት 24 በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይመራኛል፣ ልማትና መልካም አሰተዳደር ያረጋግጥልኛል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
የከተማ ነዋሪዎቹ አክለውም ምርጫ የተሻለ ሀገርን ለመገንባት እና የሰለጠነ ዴሞክራሲ መገለጫ በመሆኑ በዕለቱ ካርዱን ይዞ መብቱን እንዲጠቀም አሳስበዋል።
የአንድ ሰው ድምጽ ዋጋ እንዳለው በማመን ምርጫው ሠላማዊ ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ: አርሻል አራቦ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ
የአንድን ሀገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ትምህርትና ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ብቁ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት መስራት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)