ነገ ግንቦት 24 በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የመራጭነት ካርድ ከያዙ ቤተሰቦቻቸው ጋር በንቃት እየተጠባበቁ መሆናቸውን የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ
ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
ከዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብቶች አንዱ ምርጫ ነው ያሉት የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች፤ ነገ ሰኞ በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የመራጭነት ካርድ ከያዙ ቤተሰቦቻቸው ጋር በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተቀመጠው የጊዜ ሳሌዳ መሰረት ባለፉት ጊዜያት ለፓርቲዎች በተዘጋጀው የክርክር መድረክ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ሀሳብ በንቃት መከታተላቸው ለምርጫ ተሳትፏቸው መልካም ድባብ እንደፈጠረላቸው ጠቅሰው፤ በዚህም ይበጀናል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።
የሰላም ባለቤት ህዝቡ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸው ድርሻ እንደሚወጡ ገልፀው ሁሉም ለሰላም ዘብ መቆም እንዳለበትም ገልጸዋል።
የምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎችም በምርጫው ዕለት ይመራኛል የሚሉትን ፓርቲ በነፃነት በመምረጥ መንግስት የመመስረት ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን መጠቀም እንዳለባቸውም አስተያየት ሰጪዎቹ ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
ዘጋቢ፡ ኤደን ተረፈ አና ኤርጡሜ ዳንኤል – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
አሊያንስ አርባ ምንጭ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1462 ተማሪዎችን አስመረቀ
የአንድን ሀገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ትምህርትና ስልጠና ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ
የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ብቁ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት መስራት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)