ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጻቸውን ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ የደካ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ
ምርጫ ለአንድ ሀገር ዴሞክራሲ መጎልበትና ሉዓላዊነት ወሳኝ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።
ጣቢያችን ሁነቱን እየተከታተለ ለመዘገብ በስፍራው የተገኘ ሲሆን በዚህ ወቅት ያነጋገርናቸው የደካ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁት፤ ዜጎች ምርጫ ላይ በነቂስ መሳተፋቸው የሀገር ፍቅር መገለጫ ነው።
በሕዝብ ድምጽ የተመረጠ መንግሥት ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ የሚፈልጉትን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ እንደሆኑም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ምርጫ የዴሞክራሲ መገለጫና ሀገርን የሚያስቀጥል ሥርዓት እንደሆነም ተናግረዋል።
የወሰዱትን የመራጭነት ካርድ በጥንቃቄ ይዘው መቆየታቸውን የተናገሩት ነዋሪዎቹ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ማልደው በመነሳት ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፤ ልማትና ዕድገት ያረጋግጣል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን አስተያየት ሰጭዎቹ ተናግረዋል።
ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
የአንድ ሰው ድምፅ ትልቅ ዋጋ እንዳለው በመገንዘብ፣ ካርድ የወሰደ ዜጋ ሁሉም በዕለቱ ወጥቶ ድምጹን እንዲሰጥም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡ ሀብታሙ ታደሰ
ፎቶ፡ ኪዳኔ ተስፋዬ

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)