ወጣቱን ተጠቃሚ ያደርጋል ያልነውን መንግስት ለመምረጥ ተዘጋጅተናል – የሶያማ ከተማ ወጣቶች
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለወደፊቱ ይበጀናል ያልነውን ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ በቡርጂ ዞን የሶያማ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ።
በሶያማ ከተማ አስተዳደር የ01 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወጣት ማሻ ማርቻ እና ህርቦ አለማየሁ ለሀገራችን ልማት እና እድገት ይጠቅመናል የምንለውን ለመምረጥ ዝግጅት አድርገናል ሲሉ ተናግረዋል።
በከተማው የ 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወጣት ጥሩዬ ካሳ የእኔ አንድ ድምጽ ያለው ዋጋ ቀላል ባለመሆኑ የመምረጥ መብቴን በመጠቀም የሚያስተዳድረኝን ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ ስትል ገልጻለች።
ሌላኛው አስተያየታቸውን የሰጡን የኦቶማሎ ቀበሌ ነዋሪ ወጣት ህርብቻ ዋዮ ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብዬ የማስበውን መንግስት ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ ብሏል።
አስተያየት ሰጪዎቹ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ሀሳባቸውን አጋርተዋል።
ዘጋቢ: አሀዱ አሸናፊ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
ወጣቱን ተጠቃሚ ያደርጋል ያልነውን መንግስት ለመምረጥ ተዘጋጅተናል – የሶያማ ከተማ ወጣቶች

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)