በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የዲላ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
ህብረተሰቡ በሰላማዊ መንገድ ድምጹን በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበትም ተጠይቋል።
አገልጋይ ዘውዴ ከበደ የዲላ ከተማ ነዋሪ ናቸው። ሀገር ሰላም ሆኖ ሰላማዊ ምርጫ እንዲካሄድ በጸሎት እየተጉ ድምጻቸውን ለመስጠትም ቀኑን እየጠበቁ እንዳለ ተናግረዋል።
የሰው ልጅ ዘርቶ ማፍራት፣ ሠርቶ መብላትና ወጥቶ መግባት የሚችለው ሰላም ሲኖር ብቻ በመሆኑ ሁሉም ለሰላም የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይገባል ብለዋል።
በዲላ ከተማ በወንዶች የውበት ሳሎንና በልብስ ስፌት ሥራ ላይ የተሰማሩት ወጣት ቢኒያም ጴጥሮስና አቶ ቸርነት አለሙ፤ ይበጀኛል ይሆነናል የሚሉትን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን በመግለጽ ሁሉም ዜጋ ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቀዋል።
ምርጫ የአንድ ሀገር ዴሞክራሲ መገለጫ ነው ያለችው ደግሞ ወይዘሪት ስምረት ኢያሱ፤ ወጣቶች ለሀገራቸው የነገ መጻኢ ተስፋ በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።
ዕለተ ሰኞ ማለዳን ከነቤተሰቦቻቸው ድምጽ ለመስጠት በጉጉት እየተጠባበቁ እንዳለ የገለጹት ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አርሶአደር ታምሩ ጎበና፤ ህብረተሰቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ ድምጽ ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዘጋቢ: ውብሸት ካሳሁን – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የዲላ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

More Stories
የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ በሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት የማህበረሰቡ ተጠቃሚነትን ለማሻሻል እያከናወነ የሚገኘውን አበረታች ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለፁ
በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከጅምሩ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ