በጠቅላላ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም ዝግጁ መሆናቸውን በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ
በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ አሰተዳደር ነዋሪዎች መካከል ቄስ ምህረቱ ጋለ፣ ዜጎች በሰላም ወጥተው ድምጻቸውን እንዲሰጡና መንግስታቸውን እንዲመርጡ በመጸለይ የበኩላቸውን እየተወጡ እንደሆነ ገልጸው መብታቸውን ለመጠቀም ካርዳቸውን ወስደው ቀኑን በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሆነ አመላክተዋል።
ሌሎች ነዋሪዎች አቶ ሄኖክ አሳምነውና ኡስማን ብሩክ፤ ግንቦት 24/2018 ዓ/ም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ይሆነኛል፣ ያስተዳድረኛል ለሚሉት ፓርቲ ድምጻቸውን በመስጠት የሚመራቸውን መንግስት ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከወጣቶች መካከል ፍሬህይወት ስላሴና ተካልኝ መነሻ፤ አንድ ድምጽ መንግስትን ለመመስረት ዋጋ እንዳለው ገልጸው፤ ሰኞ ወደ ምርጫ ጣቢያቸው በመሄድ በጊዜ ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ የ2018 ዓ/ም ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ለሰላም ዘብ እንዲቆም አሳስበዋል።
ግንቦት 24/2018 ዓ/ም ሰኞ ዕለት ጠቅላላ ምርጫው የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።
ዘጋቢ: እስራኤል ቅጣው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
በጠቅላላ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም ዝግጁ መሆናቸውን በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)