የወሰድነውን የመራጭነት መታወቂያ ካርድ ተጠቅመን ድምፅ ለመስጠት እራሳችንን አዘጋጅተናል – የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች
ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው የወሰዱትን የምርጫ ካርድ በመጠቀም ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አንዳንድ የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የዘንድሮው 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሀዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ፤ በእለቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ሰዓቱንና ስርአቱን ጠብቀው የድርሻውን መወጣት እንዳለባቸውም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ምርጫ ዜጎች ለነገዋ ኢትዮጵያ ስኬት በተሻለ ይሰራል ብለው ያሰቡትን የመምረጥ እና የራሳቸውን እድል በራሳቸው የመወሰን መብታቸውን የሚያስከብሩበት ሂደት መሆኑንም ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት አንስተዋል።
ዘጋቢ፡ ሸዊት ሂርጶ

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው