የሚበጀንን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል – የማሻ ከተማ ነዋሪዎች
ይበጀኛል፣ ትዉልድን ያሻግራል እንዲሁም ሀገርን ይመራል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸዉን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን የማሻ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ የዜጎች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸው፤ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ የሀገሪቱን ሠላም፣ ልማትና አንድነት የሚያስቀጥል የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ በካርዳቸዉ ይበጀኛል፣ ትዉልድን ያሻግራል እንዲሁም ሀገርን ይመራል ላሉት ፓርቲ ድምጻቸውን እንደሚሰጡም ገልጸዋል።
የድምጽ መስጫዉ ዕለት ዜጎች ድምጻቸዉን ለሚፈልጉት ፓርቲ መስጠት እንዳለባቸዉ ያነሱት የማሻ ከተማ ነዋሪዎች፤
ምርጫዉ በሠላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ እንደ ዜጋ የድርሻቸዉን እንደሚወጡም ተናግረዋል።
ዘጋቢ: ግርማ ጮሪቶ – ከማሻ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው