የሀዋሳ ከተማ ምርጫ ክልል የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ በማሰራጨት ላይ ይገኛል
የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማድረስ ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት የሀዋሳ ከተማ የምርጫ ክልል ኃላፊ ወ/ሪት ከፊቱ ስዩም፤ በከተማዉ 308 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን እስከአሁን በ259 ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ መስራጨቱን አስታዉቀዋል።
ለቀሪ 49 የምርጫ ጣቢያዎች በነገዉ እለት እንደሚሰራጭም ተናግረዋል።
ኃላፊዋ አክለዉም፤ በስርጭት ወቅት ችግሮች እንዳይገጥሙ ከፖሊስ አካላት ጋር የቅንጅት ስራ መስራቱንም ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ባየሽ ጉልላት

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው