አስፈላጊ የምርጫ ቁሳቁሶች እየተሰራጨ መሆኑ ተገለፀ
በምርጫ ክልሉ ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እየተሰራጩ መሆኑን የሶዶ ዙሪያ 2 ምርጫ ክልል ኃላፊ አስታወቁ።
ኃላፊው ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሥርጭቱን በማከናወናቸው ምንም ዓይነት ችግር እንዳልገጠማቸው ጠቁመዋል።
የሶዶ ዙሪያ 2 ምርጫ ክልል ኃላፊ አቶ ምህረቱ ጋዴቦ በምርጫ ክልሉ 108 የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ገልፀው፤ ለሁሉም በሚባል ደረጃ አስፈላጊ የምርጫ ቁሳቁስ መሰራጨቱን ገልፀዋል።
በምርጫ ክልሉ ከሚገኙ 108 ጣቢያዎች ውስጥ በ92ቱ የመራጮች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል መከናወኑን ጠቅሰው፤ በቀሪ 16ቱ በማኑዋል መመዝገቡን አስታውቀዋል።
ለሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ ቁሳቁስ በማሰራጨት የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቋል ያሉት አቶ ምህረቱ፥ የፀጥታ አካላት ኃላፊነታቸውን መወጣታቸው ሥራው በስኬት እንዲጠናቀቅ ማድረጉን ጠቁመዋል።
በወላይታ ሶዶ ከተማ ፋና ቀበሌ ዲያስፖራ መንደር ጉጃ ኮይራ ምርጫ ጣቢያ ኃላፊ አቶ አዲሱ ጎአ በበኩላቸው ለምርጫ ጣቢያው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን መረከባቸውን ተናግረዋል።
ርክክቡን የፀጥታ አካላትን ጨምሮ መገኘት ካለባቸው አካላት ጋር በጋራ ማከናወናቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ: ካሱ ብርሃኑ

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)