በሀዲያ ዞን ሶሮ 02 ምርጫ ክልል ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያ እየተሰራጨ ይገኛል
ከነገ በስቲያ ለሚከናወነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሶሮ 02 ምርጫ ክልል ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ይገኛል፡፡
በሀዲያ ዞን ካሉ ምርጫ ክልሎች አንዱ የሆነው በሶሮ 02 ምርጫ ክልል ለሚገኙ ለሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በስፍራው ተገኝቶ መመልከት ችሏል።
በምርጫ ክልሉ 97 ምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን እስካሁን ለ50 ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ መሰራጨቱን የሶሮ 02 ምርጫ ክልል አስተባባሪ ሰላሙ ታረቀኝ ተናግረዋል።
ለቀሩት ምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ እና ነገን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ተሰራጭቶ ይጠናቀቃል ያሉት አስተባባሪዉ፤ ዝግጅቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ጠቁመዋል።
የምርጫ አስተባባሪዎችም ቁሳቁሶቹ በተገቢው እንዲደርሱ እያደረጉ መሆናቸውን አክለዋል።
የጃጁራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር ብርሃኑ ደቦጭ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ኦረንቴሽን ከመስጠት ጀምሮ ከፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ካለምንም ችግር ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የፀጥታ አካላት ተሰማርተዋል።
እስከአሁን ባለዉ በጣቢያዎቹ ምንም ስጋት እንደሌለና እስኪጠናቀቅ ድረስም ከመራጩ ህብረተሰብና ምርጫ ጣቢያዎች ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
በምርጫ ክልሉ ያሉ አብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጅታቸውን እየጨረሱ መሆናቸውም ተመላክቷል።
ዘጋቢ፡ ብዙነሽ ዘዉዱ
በሀዲያ ዞን ሶሮ 02 ምርጫ ክልል ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያ እየተሰራጨ ይገኛል

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)