በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሌሞ 01 ምርጫ ክልል ስር ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተደረገ ነው
ሀዋሳ፡ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሌሞ 01 ምርጫ ክልል ስር ለሚገኙ 140 የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭት እያከናወነ መሆኑን የሌሞ 01 ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን አሻግሬ ገለፁ።
በሌሞ 01 ምርጫ ክልል ስር 140 የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚገኙ የገለፁት አስተባባሪው፤ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭቱን በተሳካ ሁኔታ ለማሳለጥ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሚገኙም አብራርተዋል።
በምርጫ ጣቢያዎቹ 125,548 መራጮች የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን የጠቆሙት አስተባባሪው፤ 62,500 የሚሆኑት መራጮች በዲጂታል አማራጭ የተመዘገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በሌሞ ወረዳ የደማላ ባልቡላ ምርጫ ጣቢያ ትምህርት ቤት የምርጫ ጣቢያው ሀላፊ አቶ ጥጋቡ ታፈሰ፤ ለምርጫ ጣቢያው የሚሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶችን ለመረከብ በስፍራው መገኘታቸውን ጠቅሰው፤ የምርጫ ክልሉ ቁሳቁሶችን በጊዜ ተደራሽ የማድረግ ስራውን በተገቢው ሁኔታ እያካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።
ዘጋቢ: ሸዊት ሂርጶ

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው