ለቀጣይ አምስት አመታት የሚያስተዳድረንን መንግሥት ለመምረጥ ዝግጅት አድርገናል ሲሉ በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ
ምርጫው በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ጠቁመዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች በወሰዱት ምርጫ ካርድ ሀገርን የሚያስተዳድር መንግሥት ለመምረጥ ዝግጅት አድርገው ቀኑን እየተጠባበቁ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በዞኑ ከሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ ምንተስኖት ሽመክት እና አቶ አለማየሁ ጎፃ እንዲሁም ዶክተር ሜንዛ ዙትያብ እና ወ/ሮ ደብሪቱ ካናኮ በሰጡት አስተያየት፤ በወሰዱት ምርጫ ካርድ ከፊታችን ሰኞ ግንቦት 24 ወጥተው የሚያስተዳድራቸውን መንግስት ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ የወሰዱት ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በተገቢው እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩ ባለፈ፤ ሀገር የሚያስተዳድረውን መንግሥት ለመምረጥ ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
ግንቦት 24 ሁሉም ህብረተሰብ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለሀገር እና ለሕዝብ የሚጠቅመውን መንግስት በመምረጥ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አስተያየት ሰጪዎች ገልፀዋል፡፡
በሀገር ደረጃ እየተከናወነ ያለውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ይበልጥ ለማጎልበት ሁሉም ዜጋ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባውም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን ዳጉሳ – ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር መሆኑ ተገለጸ
በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ
የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለስና ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት የማጠናቀቅ ቁርጠኝነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)