በዕለቱ ህብረተሰቡ ቀጣይ ሀገሬን በስኬትና ከፍታ ማን ሊመራ ይገባል የሚለዉን አፅንዖት በመስጠት ድምፅ ሊሰጥ ይገባል – የጃጁራ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች
በምርጫዉ ዕለት ህብረተሰቡ ቀጣይ ሀገሬን በስኬትና ከፍታ ማን ሊመራ ይገባል የሚለዉን አፅንዖት በመስጠት ድምፅ ሊሰጥ እንደሚገባ በሀዲያ ዞን የጃጁራ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ከዚህ በፊትም በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ካርድ መውሰዳቸውን ገልፀው፤ በዕለቱ ተገኝተው ለመምረጥ ዝግጅታቸውን ጨርሰው በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
ከአሁን በፊት የተካሄዱትን የፖለቲካ ፖርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ በንቃት ሲከታተሉ እንደነበር አስታዉሰዋል።
የጃጁራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ለይኩን ሱልዶሎ በበኩላቸዉ፤ ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ ብሎም ቅቡልነት ያለዉ ምርጫ እንዲሆን ቅድመ ዝግጅቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ሰኞ የገበያ ዕለት ቢሆንም እንዳይኖሮ ዝግ መደረጉን የገለፁት ከንቲባው፤ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችም ከቁሳቁስ ጀምሮ ሌሎችም አስፈላጊ ግብአቶች መሟላታቸውን አመላክተዋል።
በዕለቱ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ካርድ የወሰዱ መራጮች በሙሉ በምርጫ ጣቢያቸው ተገኝተዉ ይሆነኛል ብለዉ ለሚያምኑትን የፖለቲካ ፓርቲ ድምፅ በመስጠት እንዲመርጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡ ብዙነሽ ዘዉዱ
በዕለቱ ህብረተሰቡ ቀጣይ ሀገሬን በስኬትና ከፍታ ማን ሊመራ ይገባል የሚለዉን አፅንዖት በመስጠት ድምፅ ሊሰጥ ይገባል – የጃጁራ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው