ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ቁሳቁሶችን ለምርጫ ጣቢያዎች እያሰራጨ መሆኑን የአማሮ ኬሌ ምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት አሰታወቀ
በምርጫ ክልሉ ከ87 ሺህ በላይ መራጮች ተመዝግበው ካርድ መውሰዳቸው ተመላክቷል፡፡
የአማሮ ኬሌ ምርጫ ክልል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተካበ ቦጋለ እንደተናገሩት፤ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ መነሻ ከመራጮች ምዝገባ አንስቶ በምርጫ ክልሉ በቂ ዝግጅት ተደርጓል።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች ለምርጫ ክልሉ መላካቸውን የተናገሩት ኃላፊው፤ አሁን ላይ የምርጫ ቁሳቁሶችን ለመምርጫ ጣቢያዎች እያሰራጩ እንደሆነ አመላክተዋል።
በአማሮ ኬሌ ምርጫ ክልል 1 መቶ 17 ምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን በጣቢያዎቹ 87 ሺህ 1 መቶ 1 መራጮች ተመዝግበው ካርድ መውሰዳቸውንም ገልጸዋል።
ከተመዘገቡ መራጮች መካከል 44 ሺህ 6 መቶ 68 ወንዶች ሲሆኑ 42 ሺህ 5 መቶ 6 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን አቶ ተካበ ተናግረዋል።
ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች መመዝገባቸው ይታወቃል።
ዘጋቢ: እስራኤል ቅጣው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው