በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚበጃቸው ፓርቲ ለመምረጥ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን የጂንካ ነዋሪዎች ገለጹ

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚበጃቸው ፓርቲ ለመምረጥ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን የጂንካ ነዋሪዎች ገለጹ

ሀዋሳ: ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የፊታችን ሰኞ በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚበጃቸው ፓርቲ ለመምረጥ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን በኣሪ ዞን የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

ምርጫው ፍትሃዊና ሰላማዊ ሆና እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24 ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስፈላጊ ዝግጅቶች ሲከናወኑ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው።

በእለቱ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ይበጀኛል የሚሉትን ፓርቲ በመምረጥ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን በኣሪ ዞን የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች በተለይ ለደቡብ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት በሰጡት አስተያየት አመላክተዋል።

ምርጫው ፍትሃዊና ዲሞክሬሲያዊ በሆነ መልኩ ይጠናቀቅ ዘንድ ግንቦት 24 ዕለተ ሰኞን በጉጉት እየተጠባበቁ መሆኑን ጠቅሰው፥ በጠዋት ድምጻቸውን ሰጥተው ለመመለስ ማቀዳቸውንም ገልጸዋል።

ለምርጫው በሰላም መጠናቀቅ የድርሻውን መወጣት ይገባልም ብለዋል ነዋሪዎቹ።

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስፈላጊ ግብዓቶች በመላው የዞኑ አካባቢዎች እንዲሰራጭ መደረጉንም ለመረዳት ተችሏል።

ዘጋቢ: ወንድሜነህ አድማሱ – ከጅንካ ጣቢያችን