‎‎‎የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአርባምንጭ ምርጫ ክልል የቁሳቁስ ስርጭት እያደረገ መሆኑን ገለፀ

‎‎የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአርባምንጭ ምርጫ ክልል የቁሳቁስ ስርጭት እያደረገ መሆኑን ገለፀ

‎ሀዋሳ: ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ምርጫ ክልል ለ227 (ንዑስ ምርጫ ጣቢያዎችን ጨምሮ/ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ 2 ንዑስ እና አርባምንጭ ከተማ 3 ንዑስ)የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭት እያደረገ መሆኑ አስታውቋል።

‎በአርባምንጭ የምርጫ ክልል ለሚገኙ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ስራ በስኬት እየተከናወነ መሆኑን ነው የምርጫ ክልሉ አስተባባሪው የገለፁት።

‎የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ አቶ ታምሩ ጥበቡ ፥ በከተማው የምርጫ ክልል ስር በአጠቃላይ 227 ምርጫ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ጠቁመው፥ በእነዚህ ጣቢያዎች ለምርጫው ሂደት አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ተደራሽ የማድረግ ስራ ከትላንት ጀምሮ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

‎እስካሁን ባለው ሂደት የጋጮ ባባ ወረዳ 53 የምርጫ ጣቢያ ቁሳቁስ መላኩን ጠቁመው፥ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ለ52 የምርጫ ጣቢያ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ እየተሠራጨ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ለአርባምንጭ ከተማ ለ117 የምርጫ ጣቢያ ቁሳቁስ እስከ ነገ አሠራጭቶ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

‎ቁሳቁሶቹን ለምርጫ ጣቢያዎቹ የማድረሱ ተግባር ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ያለምንም መስተጓጎል እየተከናወነ መሆኑንም አስተባባሪው አክለው ገልጸዋል።

‎ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ