ዒድ አል አደሀ በዓል በሂጅራ ዘመን አቆጣጠር በዙልሂጃ ወር ዘጠነኛው ቀን ላይ የሚከበር በዓል ነው።
በዓሉ ነብዩላህ ኢብራሂም ልጃቸውን ኢስማኤልን በፈጣሪ ትዕዛዝ በሆነ ጊዜ በስጦታ የቀረበላቸውን የጀነት በግ በማሰብ የእርድ ስነ ስርዓት የሚፈፀምበት በዓል ነው፤ ይህ የእርድ ስነ ስርዓት አዱሁያ ይባላል።
አዱህያ አንድ ሰው ያረደውን ስጋ ለሶስት በመክፈል አንድ ሶስተኛው ለራሱ አንድ ሶስተኛ ለሚስኪን የቀረውን አንድ ሶስተኛ ደግሞ እዚያው እርድ ቦታ ላይ ከጎረቤት ጋር ተሰባስቦ በመብላት የሚፈፀም ስነ-ስርዓት ነው።
በዒድ ዓል አደሀ የአባት ቁርጠኝነት የልጅ ታዛዥነትና የፈጣሪ እዝነት ከፍ ብሎ የታየበት በመሆኑ በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በጣም በልዩነት ድምቀት የሚከበር በዓል ነው ።
በዓሉ በሀጅ ስነ-ስርዓት በፆምና በጋራ በሚደረግ የዒድ ሶላት የሚከበር ሲሆን፣ ዘመድ አዝማድን በመጎብኘት፣ ስጦታዎችን በመለዋወጥና በጋራ በመመገብ ይከበራል።
በዓሉን ትልልቅ የቤተሰብ ጉብኝቶችን በማድረግ፣ ለበዓሉ ተብለው የሚዘጋጁ ልዩ ባህላዊ ምግቦችንና ጣፋጮችን በማጋራት በህዝበ ሙስሊሞች ዘንድ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል።
የሶላት ስነ-ስርዓትም፣ አማኞቹ በማለዳው ተነስተው ውበትን ጠብቆ ወደ መስጊድ ወይም የዒድ መስገጃ ቦታ በመሄድ በጋራ ሶላት ማከናወን እና አላህን ማመስገንን ይጨምረል።
የዒድ አል-አደሀ በዓል በኢትዮጵያ በተለይም እንደ ወሎ፣ ሐረር እና ጅማ ባሉ አካባቢዎች መንዙማን፣ ሀድራን እና የነብዩ ሙሐመድን ታሪክ የሚዘክሩ ውዳሴዎችን በማቅረብ እጅግ ደምቆ ይከበራል።
በዓሉ የይቅርታና የእዝነት በመሆኑ የተቀያየሙ ሰዎች የሚታረቁበት ወቅት ስለመሆኑም የቤተ-እምነቱ መንፈሳዊ መጽሐፍት እና ሌሎችም በመረጃቸው ይጠቅሳሉ።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሐ (ዐረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ “ዒድ ሙባረክ”
በመስከረም አበበ

More Stories
ተአምረኛው የዘምዘም ውሃ
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በጋሞ ዞን ጨንቻ እና አካባቢው የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ተካሂዷል