ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ እንዲከናወን መወሠኑ ይታወቃል።
በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ በዕለቱ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ለመንግሥታዊ እና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።
በዚህም መሠረት:-
👉ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣
👉ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ፤
የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።
👉የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው