1ሺ 447ኛው ኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ
የጂንካ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ኡመርዲን ግርማ እንኳን ለ1ሺ 447ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሰን መልዕክት ለእምነቱ ተከታዮች አድርሰው፥ በዓሉን ስናከብር ለአንድነትና ለሠላም ልዩ ትኩረት ልንሰጥ ይገባናል ብለዋል።
የበዓሉ ዋና መልዕክትም የሚያረጋግጥልን ይህንኑ በመሆኑ ለተቸገሩ ወገኖች ያለንን አካፍለን ልንሰጥ ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል።
የኣሪ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ጀማል መሐመድ በዓሉን ስናከብር ከሃይማኖታዊ አስተምህሮ በተጨማሪ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች አካፍለን እየሰጠን መሆን አለበት ብለዋል።
የበዓሉ ታዳሚ አንዳችን ለሌላችን አቅም ሆነን በህብረት ቆመን አንድነታችን አጽንተን ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ከፍታ ልናሸጋግር ይገባናል ሲሉም አቶ ጀማል መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ግንንቦት 24/2018 ዓ/ም የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መላው የሙሲሊሙ ማህበረሰብ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ ለእምነቱ ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
በዓሉ ሲከበር ከቀድሞ ይልቅ አንድነትትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን በማጎልበት መሆን እንዳለበት ጠቁመው፥ ሀገራችን ብዙ ህብረ ብሔራዊ ቀለምና የሀይማኖት ተከታዮች ያሉበት በመሆኑ ይህ ደግሞ ለአንድነትና በጋራ ለበልፀግ ትልቅ አቅም እንጂ ለአለመግባባት መንስኤ ሊሆን አይገባም ብለዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው